ቀስተ ደመና ሬድዮ ፣ ግራፔካ (Reseach and Actoin Group for peace in Ethiopia and in the Horn of Africa – GRAPECA ) በኢትዮጵያ ሰላም ለመገንባት ከነበረው አጠቃላይ የስራ እቅድ አካል ነበር። ስርጭቱንም በመስከረም 1990 ዓ/ም ጀመረ። በሳምንት አንድ ቀን የአንድ ሰዓት ፕሮግራም ወደ ኢትዮጵያ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ የሚሰራጨው የራዲዮ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ተፈራ አስማረ ነበር።
ተፈራ አስማረ የኢትዮጲስ ዋና አዘጋጅ፣ በህዳር 1985 ዓ/ም « ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት » እና « የሀሰት ወሬ » በማሰራጨት በሚል ምክንያት ከታሰሩት ጋዜጠኞች አንዱ ነበር። የሁለት ዓመት እስራት ተፈርዶበት ከተለቀቀ በሁዋላ፣ ሃገር ውስጥ በነጻነት የጋዜጠኝነት ሙያውን መቀጠል ባለመቻሉ ወደ ኔዘርላንድስ ለመሰደድ ተገደደ። ተፈራ አስማረ የቀሰተ ዳመና ዋና አዘጋጅ በመሆን ከ1990 እስከ 1995 ዓ/ም ሙያውን ለዚህ ነጻ ራዲዮ ያዋለ ጋዜጠኛ ነበር። በ 1996 ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል።

ዋና ዋና ይዘቶች

በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከሚያቀርባቸው ዜና፣ ትንተናና ቃለ መጠይቆች በተጨማሪ፣ የራዲዮኑ ዋና ዋና ይዘቶች ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብትና የህግ የበላይነት መከበር፣ በህዝቦች መካከል በእኩልነት አብሮ መኖር ዙሪያ በቀላል አማርኛ የተሰናዱ ተከታታይ ፕሮግራሞች ነበሩት። “የሰብአዊ መብቶች አዋጅ ለማስተዋወቅ ፣ አዋጁ ምን ይላል በሚለው ጥያቄ ዙሪያ የተሰናዱ ፕሮግራሞች አንዱ ምሳሌ ነው። በነጻ ምርጫ ዙሪያ የተሰናዳ ትምህርታዊ ፕሮጋምም ስለ ነጻ ምርጫ ግንዛቤ እንዲኖር የበኩሉን አስትዋጽኦ አድርጓል። “ወንድማማች ህዝብ” የተሰኘው ፕሮግራም በብሄሮች መሃከል እኩልነትና ወንድማማችነት እንዲሰፍን፣ ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብት ለሚከበረበት ስርአት አብሮ መታገል እንድሚያስፈልግ የተለያዩ ፕሮግራሞች አቅርቦአል። በዚህ ክፍል ውስጥ የቀረቡት፣ የነገደ ትችቶችና ትንተናዎች ብቻ ናቸው።

የራዲዮኑ ባለቤት:  ግራፔካ

የጀመረበት ቀን:  መስከረም 1990 ዓ/ም

ዲሬክተር:  ነገደ ጎበዜ

ዋና አዘጋጅ:  ተፈራ አስማረ

ስርጭት:  ኢትዮጵያ፣ ምስራቅ አፍሪካ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ

ቋንቋ:  አማርኛ

ቀስተ ደመና ሬድዮ ፣ ግራፔካ በኢትዮጵያ ሰላም ለመገንባት ከነበረው አጠቃላይ የስራ እቅድ አካል ነበር። ስርጭቱንም በመስከረም 1990 ዓም ጀመረ። በሳምንት አንድ ቀን የአንድ ሰዓት ፕሮግራም ወደ ኢትዮጵያ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ የሚሰራጨው የራዲዮ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ተፈራ አስማረ ነበር።
ተፈራ አስማረ የኢትዮጲስ ዋና አዘጋጅ፣ በህዳር 1985 ዓም « ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት » እና « የሀሰት ወሬ » በማሰራጨት በሚል ምክንያት ከታሰሩት ጋዜጠኞች አንዱ ነበር። የሁለት ዓመት እስራት ተፈርዶበት ከተለቀቀ በሁዋላ፣ ሃገር ውስጥ በነጻነት የጋዜጠኝነት ሙያውን መቀጠል ባለመቻሉ ወደ ኔዘርላንድስ ለመሰደድ ተገደደ። ተፈራ አስማረ የቀሰተ ዳመና ዋና አዘጋጅ በመሆን ከ1990 እስከ 1995 ዓም ሙያውን ለዚህ ነጻ ራዲዮ ያዋለ ጋዜጠኛ ነበር። በ 1996 ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል።

ዋና ዋና ይዘቶች

በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከሚያቀርባቸው ዜና፣ ትንተናና ቃለ መጠይቆች በተጨማሪ፣ የራዲዮኑ ዋና ዋና ይዘቶች ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብትና የህግ የበላይነት መከበር፣ በህዝቦች መካከል በእኩልነት አብሮ መኖር ዙሪያ በቀላል አማርኛ የተሰናዱ ተከታታይ ፕሮግራሞች ነበሩት። “የሰብዊ መብቶች አዋጅ ለማስተዋወቅ ፣ አዋጁ ምን ይላል በሚለው ጥያቄ ዙሪያ የተሰናዱ ፕሮግራሞች አንዱ ምሳሌ ነው። በነጻ ምርጫ ዙሪያ የተሰናዳ ትምህርታዊ ፕሮጋምም ስለ ነጻ ምርጫ ግንዛቤ እንዲኖር የበኩሉን አስትዋጽኦ አድርጉዋል። “ወንድማማች ህዝብ” የተሰኘው ፕሮግራም በብሄሮች መሃከል እኩልነትና ወንድማማችነት እንዲሰፍን፣ ዲሞክራሲና ሰብአዊ ለሚከበረበት ስርአት አብሮ መታገል እንድሚያስፈልግ የተለያዩ ፕሮግራሞች አቅርቦአል። በዚህ ክፍል ውስጥ የቀረቡት፣ የነገደ ትችቶችና ትንተናዎች ብቻ ናቸው።


የራዲዮኑ ባለቤት:  ግራፔካ

የጀመረበት ቀን:  መስከረም 1990

ዲሬክተር:  ነገደ ጎበዜ

ዋና አዘጋጅ:  ተፈራ አስማረ

ስርጭት:  ኢትዮጵያ፣ ምስራቅ አፍሪካ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ

ቋንቋ:  አማርኛ

RAC 1990 Ethiopian Calendar

ቀስተ ደመና ሬድዮ | 1990 ዓ/ም

RAC 2000

ቀስተ ደመና ሬድዮ | 2000 እንደ አውሮፓ አቆጣጠር

Privacy Preference Center