እንደተመቻት የምትወጣ ነፃ ጋዜጣ
በአብዮቱ ዘመን የፖለቲካ የመስመር ልዩነትን በተመለከት በሃገሪቱ ዘስጥ በአጠቃላይ፣ በተለይም በመኢሶናን በኢህአፓ መሃከል ይፋ ክርክሮች ውስጥ ይካሄድ ነበር። ይህንንም ለማበረታታት ዳንኤል ታደሰና ነገደ ጎበዜ፣ ፈረንሳይ አገር ተማሪዎች በነበሩበት ጊዜ፣ የማታመልጣቸውን ‘ካናር አንሼኔ’ « Le Canard enhaîné « በምትባል አሽሟጣጭ ሳምንታዊ ጋዜጣ መልክ አንድ ቋሚ ጋዜጣ ለመጀመር ወሰኑ፡፡
ስሙን በሚመለከት ዳንኤል ያቀረበው ሃሳብ ‘ሂስ’ እንበላት ሲሆንነገደ ደግሞ በዛችው « በካናር አንሼኔ » መንፈስ ለምን ‘ሽሙጥ’ አንላትም ብሎ በዚህ ተስማሙ፡፡ ከዚያም በየስንት ጊዜ ትወጣ? በየአስራ አምስት ቀኑ? ሳምንታዊ ወይስ ወርሃዊ ትሁን የሚለው ጥያቄ ተነስቶ ዳንኤል ‘እንዳመቻት የምትወጣ ነጻ ጋዜጣ’ ትባል ስላለ በዚሁ ተውሰነ፡፡
እንደ መነሻ የተወሰደው ሃሳብ፣ አንድ ፊውዳል ባላባት አገር ቤት ሆነው፣ ለንደን ለሚኖሩት ለአልጋ ወራሹ በሚጽፉት ደብዳቤና የፊውዳሉ ሰፈር መሪዎች ደርግን ለመጣል የሚከተሉትን ስትራቴጂ – በዚህ ውስጥ ደግሞ የኢህአፓን አካሄድ – በሚዘረዝር መልክ ስራው ተጀመረ፡፡ ይህም ሆኖ የፊውዳሉ ባላባት ለአልጋ ወራሹ በሚልኩት ደብዳቤ የታተሙት፣ ከጥር 1968 እስከ የካቲት 1969፣ ሶስት ቁጥሮች ብቻ ነበሩ፡፡ ሽሙጥም ብዙ ሳትሄድ በደርግና በመኢሶን መክከል በተፈጠረው ልዩነት፣ መኢሶን ወደ ህቡእ ትግል ገባ። ዳንኤልም ታደሰም ገጠር ገብቶ ወዲያው ህይወቱን ለኢትዮጵያ አብዮት በ1969፣ ስለተሰዋ ሽሙጥ የምትቀጥልበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ ሆኖም፣ ሁለት የሽሙጥ ቁጥሮች በነገደ ተዘጋጀው አሉ። አንድኛው ‘አልበዛም? ዴሞክራሲስ በትግላችን!!’ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ‘የኛ ሰው በባድሜ’ ናቸው፡፡
የጀመረበት ቀን: ጥር 1968 ዓ/ም
የሽሙጥ አዘጋጆች: ዳንኤል ታደሰና ነገደ ጎበዜ
ስርጭት: ኢትዮጵያ
ቋንቋ: አማርኛ
የመጨረሻ ቁጥር: ነሃሴ 1994 ዓ/ም