አብዮታዊት ኢትዮጵያ ከ1968 እስከ 1969 ዓም ድረስ በህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዚያያዊ ጽህፈት ቤት፣ በፍልስፍና ማስፋፊያና ማስታወቂያ ኮሚቴ እየታተመ በወር ሁለት ጊዜ የሚወጣ መጽሄት ነበር። ጽህፈት ቤቱ በሚያዝያ ወር 1968 ዓም በአዋጅ ሲቋቋም፣ በደርግና በተራምጅ ምሁራን መካከል በብሄራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም፣ በዲሞክራሲ መብቶች መለቀቅ፣ በብሄሮችና በኤርትራ ጥያቄ ላይ የፖሊሲ ለውጥና፣ እንዲሁም ጊዚያዊ ጽህፈት ቤቱ ከደርግና ከመንግስት ተቋማት ነጻ ሆኖ እንዲሰራ በተደርሰው ስምምነት ነበር።
አባሎቹም ከተለያዩ አምስት የማርክሲስት ሌኒኒስት ድርጅቶች (መኢሶን፣ ወዝ ሊግ፣ ማሌሪድ፣ ኢጭአትና ሰደድ)እና ተራማጅ ምሁራን ግለሰቦች የተውጣጡ ሲሆኑ፣ የጽህፈት ቤቱ ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ የዲሞክራሲ መብቶች ስራ ላይ የሚውልበትን መመሪያ ማዘጋጀት፣ የህብረተሰባዊነት ፍልስፍና ለማስፋፋት የሚረዱ ጽሁፎችን ማቅረብና ህዝባዊ ድርጅቶች እንዲጠናከሩ ማገዝ የሚሉት ይገኙበታል። ጽህፈት ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ እስከ ነሃሴ 1969 ዓ/ም ድረስ በፕሬዝደንትነት የመራው ሃይሌ ፊዳ ሲሆን፣ ነገደ ጎበዜ የፍልስፋና ማስፋፊያና የማስታወቂያ ኮሚቴ ፕሬዝደንት በመሆን የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሰርቷል። በደርግና በተራማጆች መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት፣ በተለይም በጽህፈት ቤቱ የረቀቀውን የዲሞክራሲ መብቶች የመልቀቅ ጉዳይ ደርግ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ ተራማጆችና ደርግ አብረው መቀጠል የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጠረ።
መኢሶንም ደርግን በሚመለከት ይከተል የነበረውን ሂሳዊ ድጋፍ የፖለቲካ መስመሩን አነሳ፣ የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽህፈት ቤትንም በነሃሴ 1969 ዓ/ም ለቀቀ። ከሚያዝያ 1968 እስከ ነሃሴ 1969 ዓ/ም የወጡት የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ቁጥሮች 30 ነበሩ። መኢሶን ከለቀቀ በሁዋላ አብዩታዊት ኢትዮጵያ መታተሙን ለተወሰነ ጊዜ ቀጥሏል። ጽህፈት ቤቱ ሙሉ በሙሉ በደርግ ቁጥጥር ስር ውሎ በታህሳስ 1972 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰራተኛ ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን ተተክቷል።
አሳታሚ: የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት፣ በፍልስፍና ማስፋፊያና ማስታወቂያ ኮሚቴ
የጀመረበት ቀን: 1968 ዓ/ም
ዋና አዘጋጅ: ነገደ ጎበዜ
ስርጭት: ኢትዮጵያ
ቋንቋ: አማርኛ
አብዮታዊት ኢትዮጵያ ከ1968 እስከ 1969 ዓም ድረስ በህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዚያያዊ ጽህፈት ቤት፣ በፍልስፍና ማስፋፊያና ማስታወቂያ ኮሚቴ እየታተመ በወር ሁለት ጊዜ የሚወጣ መጽሄት ነበር። ጽህፈት ቤቱ በሚያዝያ ወር 1968 ዓም በአዋጅ ሲቋቋም፣ በደርግና በተራምጅ ምሁራን መካከል በብሄራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም፣ በዲሞክራሲ መብቶች መለቀቅ፣ በብሄሮችና በኤርትራ ጥያቄ ላይ የፖሊሲ ለውጥና፣ እንዲሁም ጊዚያዊ ጽህፈት ቤቱ ከደርግና ከመንግስት ተቋማት ነጻ ሆኖ እንዲሰራ በተደርሰው ስምምነት ነበር።
አባሎቹም ከተለያዩ አምስት የማርክሲስት ሌኒኒስት ድርጅቶች (መኢሶን፣ ወዝ ሊግ፣ ማሌሪድ፣ ኢጭአትና ሰደድ)እና ተራማጅ ምሁራን ግለሰቦች የተውጣጡ ሲሆኑ፣ የጽህፈት ቤቱ ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ የዲሞክራሲ መብቶች ስራ ላይ የሚውልበትን መመሪያ ማዘጋጀት፣ የህብረተሰባዊነት ፍልስፍና ለማስፋፋት የሚረዱ ጽሁፎችን ማቅረብና ህዝባዊ ድርጅቶች እንዲጠናከሩ ማገዝ የሚሉት ይገኙበታል። ጽህፈት ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ እስከ ነሃሴ 1969 ድረስ በፕሬዝደንትነት የመራው ሃይሌ ፊዳ ሲሆን፣ ነገደ ጎበዜ የፍልስፋና ማስፋፊያና የማስታወቂያ ኮሚቴ ፕሬዝደንት በመሆን የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሰርቷል። በደርግና በተራማጆች መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት፣ በተለይም በጽህፈት ቤቱ የረቀቀውን የዲሞክራሲ መብቶች የመልቀቅ ጉዳይ ደርግ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ ተራማጆችና ደርግ አብረው መቀጠል የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጠረ።
መኢሶንም ደርግን በሚመለከት ይከተል የነበረውን ሂሳዊ ድጋፍ የፖለቲካ መስመሩን አነሳ፣ የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽህፈት ቤትንም በነሃሴ 1969 ዓም ለቀቀ። ከሚያዝያ 1968 እስከ ነሃሴ 1969 ዓም የወጡት የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ቁጥሮች 30 ነበሩ። መኢሶን ከለቀቀ በሁዋላ አብዩታዊት ኢትዮጵያ መታተሙን ለተወሰነ ጊዜ ቀጥሏል። ጽህፈት ቤቱ ሙሉ በሙሉ በደርግ ቁጥጥር ስር ውሎ በታህሳስ 1972 ዓም በኢትዮጵያ ሰራተኛ ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን ተተክቷል።
አሳታሚ: የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት፣ በፍልስፍና ማስፋፊያና ማስታወቂያ ኮሚቴ
የጀመረበት ቀን: 1968 ዓም
ዋና አዘጋጅ: ነገደ ጎበዜ
ስርጭት: ኢትዮጵያ
ቋንቋ: አማርኛ





























