የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን ) የውጭ አካል በ1985 ዓ/ም ባደረገው ልዩ ስብሰባ፣ ስለ አገሪቱና ስለ ድርጅቱ አጠቃላይ ሁኔታ ውይይት አድርጎ፣ ድርጅቱ ለዲሞክራሲ የሚያደረገውን ትግል ለማስተዋወቅ፣ በውጭ አገር የሚወጣ አንድ የአማርኛ ጋዜጣ እንዲዘጋጅ ወሰነ። ይዘቱን በተመለከተ፣ ጋዜጣው ከአንድ ፓርቲ ልሳን ለየት ባለ መልክ በልዩ ልዩ አምዶች ሥር ዲሞከራሲያዊ ውይይቶች እንዲስፋፉ ለማገዝ የታቀደ ነበር። ስሙም “ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ” ተባለ። ከጋዜጣው ስም ስር “በመኢሶን የውጭ አካል የሚዘጋጅ ነፃ ጋዜጣ“ የሚል ሃረግ እንዲጨመርበት ተደረገ። ጋዜጣው ከ1977 ዓም ጀምሮ በሁለት ወር አንዴ እየወጣ ፣ በአሜሪካ ዶላር 50 ሳንቲም ይሸጥ ነበር። ጋዜጣው የተለያዩ አምዶችና ትችት፣ ከታሪክ ገጾች፣ ከአካባቢያችን፣ ዓለም አቀፍ፣ ነፃ ዓምድ፣ ኪነ ጥበብ፣ ከመጽሃፍትና ከድርሰቶች የሚሉ ዓምዶች ነበሩት። ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ በተከታታይ ለሰባት ዓመታት ከወጣ በሁዋላ፣ የመጨረሻውን እትም፣ ቁጥር 30ን በመጋቢት/ ሚያዝያ 1983 ዓ/ም አውጥቶ ቆሟል።
አሳታሚ: መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ የውጭ አካል
የጀመረበት ቀን: 1985 ዓ/ም
ዋና አዘጋጅ: አንድርጋቸው አሰግድ
ስርጭት: አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ
ቋንቋ: አማርኛ
የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን ) የውጭ አካል በ1985 ዓም ባደረገው ልዩ ስብሰባ፣ ስለ አገሪቱና ስለ ድርጅቱ አጠቃላይ ሁኔታ ውይይት አድርጎ፣ ድርጅቱ ለዲሞክራሲ የሚያደርገውን ትግል ለማስተዋወቅ፣ በውጭ አገር የሚወጣ አንድ የአማርኛ ጋዜጣ እንዲዘጋጅ ወሰነ። ይዘቱን በተመለከተ፣ ጋዜጣው ከአንድ ፓርቲ ልሳን ለየት ባለ መልክ በልዩ ልዩ አምዶች ሥር ዲሞከራሲያዊ ውይይቶች እንዲስፋፉ ለማገዝ የታቀደ ነበር። ስሙም “ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ” ተባለ። ከጋዜጣው ስም ስር “በመኢሶን የውጭ አካል የሚዘጋጅ ነፃ ጋዜጣ“ የሚል ሃረግ እንዲጨመርበት ተደረገ። ጋዜጣው ከ1977 ዓም ጀምሮ በሁለት ወር አንዴ እየወጣ ፣ በአሜሪካ ዶላር 50 ሳንቲም ይሸጥ ነበር። ጋዜጣው የተለያዩ አምዶችና ትችት፣ ከታሪክ ገጾች፣ ከአካባቢያችን፣ ዓለም አቀፍ፣ ነፃ ዓምድ፣ ኪነ ጥበብ፣ ከመጽሃፍትና ከድርሰቶች የሚሉ ዓምዶች ነበሩት። ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ በተከታታይ ለሰባት ዓመታት ከወጣ በሁዋላ፣ የመጨረሻውን እትም፣ ቁጥር 30ን በመጋቢት/ ሚያዝያ 1983 አውጥቶ ቆሟል።
አሳታሚ: መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ የውጭ አካል
የጀመረበት ቀን: 1985 ዓም
ዋና አዘጋጅ: አንድርጋቸው አሰግድ
ስርጭት: አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ
ቋንቋ: አማርኛ















