1952 – 1977 ዓ/ም / 1960 – 1985 (ግሬጎሪያን)
በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር የተጠነሰሰው፣ በ1950 ዓ/ም በብራስልስ ከተማ በተክሄደው የዓለም አቀፍ ኤግዚብሽን በተካሄደበት ወቅት ነበር። በዘመኑ በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ ተማሪዎች ስለነበሩ ምናልባትም ኤግዚቢሽኑን ለመጎብኘት መጥተው በዚህ አጋጣሚ ማህበር ለማቋቋም ፍላጎታቸውን ገልጸው ይሆናል። ለማንኛውም ማህበር ለማቋቋም ተስማሙ።
ከአንድ ዓመት በኋላ፣ በ1951 ዓም፣ ፓሪስ ላይ ተሰብስበው በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማሀበር ለማቋቋም ወሰኑ። ህገ ማህበር ያሚያረቅ ኮሚቴም አቋቁመው ተለያዩ። በ1952 ዓም ቦን (ጀርመን) ላይ በተደረገው ጉባኤ፣ ህገ ማህበሩ ፀድቆ የመጀመሪያው በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ጉባኤ በ1953 ዓ/ም በፈረንሳይ አገር በፓሪስ ከተማ ተካሄደ። ማህበሩም በንጉሰ ነገሥቱ የበላይ ጠባቂነትና፣ ለጉባኤው ማካሄጃ የሚያስፈልገውን ወጪ (መጓጓዣ፣ መቆያና የመሳሰሉት) በመንግስት ባጀት እየተሸፈነለት ቀጠለ።
የምህበሩም አላማ፣
- በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎችን መብት መጠበቅ
- ስለ ሃገር ሁኔታ መወያየትና እነዚህንም ጉዳዮች ከግብ የሚደርሱበትን መንገድ መፈለግ
- እውቀት የማስፋፋትና የመለዋወጥ፣ የአንድነት መንፈስ በተማሪዎች መካከል እንዲጠነክር ማድረግ፣ የአለም ሁኔታን እያጠኑ፣ የሚደረገውን መለዋወጥ ማጥናት
- በልዩ ልዩ አገሮች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ጋር መተዋወቅ፣ ሃሳብ ለሃሳብ መለዋውጥና መግባባትን መፍጠር ነበሩ።
ውይይት ለማዳበርና ሃሳቦች በነፃ እንዲንሸራሸሩ፣ አኢተማ በ 1954 ዓ/ም ባደረገው ዓመታዊ ጉባኤ፣ ማሀበሩ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የሚወጣ መጽሄት እንዲኖረውና ስሙም “ታጠቅ” እንዲባል ወሰነ። መጽሄቱም በሃሳብ ነጻነት ላይ የተመሰረተና የሚታተመውም በአማርኛ፣ ከአሰፈለገም በእንግሊዘኛ እንዲሆን ተስማምቶ አዘጋጅ የመጽሄት ቦርድ አቋቋመ።
በ1950ዎቹ ዘመን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል የተፋፋመበትና የኢምፔሪያሊዝምን መስፋፋት የሚታገሉ ሃይሎች ብቅ ያሉበት ወቅት ነበር። ይህም በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ጉባኤዎች እየተንጸባረቀ መጣ።
ቀስ በቀስም፣ ማህበሩ በአንድ በኩል መሰረታዊ ለውጥ በሚፈልጉና፣ በሌላ በኩል ጥገናዊ ለውጥ በሚሉ መሃከል ልዩነት ተፈጠረ።
በሁለቱ መስመሮች መካከል የተፋፋሙ ውይይቶች ይካሄዱ ነበር። በዚህም ወቅት፣ በምርምርና ጥናት ላይ የተመረኮዙ ስለ ኢትዮጵያ ፊውዳል ህብረተሰብ ምንነት (በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በአገዛዝ ሥርአት ወዘተ) ላይ ያተኮሩ ጽሁፎች ይቀርቡ ነበር። በተጨማሪም በኢምፔሪያሊዝም ብዝበዛና የበላይነት ጥያቄዎች ላይም ጥናቶች ይቀርቡ ነበር።
እስከ 1957 የጥገና ለውጥ መስመር የበላይነቱ ይዞ ቢቆይም፣ በዚሁ ዓመት በቪያና 5ኛ ጉባኤ ላይ፣ ማህበሩ በአብዛኛ ድምጽ ተደግፎ ፀረ ፊውዳል፣ ፀረ ኢምፔሪያሊስት የሚል አቋም ያዘ። ከዚህም ጉባኤ በሁዋላ፣ በተከታታይ በተደረጉት አመታዊ ጉባኤዎች (6ኛው እንግሊዝ አገር ፣ 7ኛው በፈረንሳይ አገር ) ማህበሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ዋና ጠላቶች ፊውዳሊዝምና ኢምፒሪያሊዝም ናቸው ብሎ በግልጽ ወጣ። ኢትዮጵያን ከባላባትዊ ስርአትና ከኢምፔሪያሊዝም ቀንበር ለማላቀቅ የሚችለው የተባበረ የሰራተኛውና የገበሬ ትግል መሆኑንንና፣ አገሪቷም መተዳደር ያለባት በህዝባዊ መንግስት መሆኑን በይፋ ያሳወቀበት ወቅት ተከሰተ።
በቀጠሉት አመታት፣ በጥናት ላይ የተመሰረቱ ለምሳሌ ምን አይነት ለውጥ በኢትዮጵያ? ለውጥስ እንዴት ይመጣል ? የተማሪስ ሚና ምንድነው ? በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በማህበሩ ውስጥ ውይይቶችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ከታጠቅ የቴዎሪ መጽሄት በተጨማሪ የትንተና፣ የሃሳብ መግለጫና ጊዚያዊ ዜናዎችን ያያዘ፣ በወር አንድ ጊዜ የሚወጣ መጽሄት እንዲጀመር የአኢተማ 7ኛው ጉባኤ ወሰነ ። በዚህ ውሳኔም በመመርኮዝ “ ትግላችን “ የተባለው መጽሄት በ1959 ዓ/ም ተጀመረ። ከአምስት ዓመት በኋላ በ1965 ዓ/ም ፣ ”የትግላችን ዜና ” የሚል መጽሄት፣ ዜና ላይ ያተኮረ መጽሄት ማውጣት ጀመረ።
በማህበሩ አባላት መካከል እስከ 1965 ፣ ማለትም እስከ 13ኛ ዓመታዊ ጉባኤ ድረስ፣ በፀረ ፊውዳል፣ በፀረ ኢምፔሪያሊስትና በብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት አስፈላጊነት ጥያቄ ዙሪያ አጠቃላይ ስምምነቶች ነበሩ። ይሁን እንጂ፣ በትግል ታክቲክ ደረጃ ከፍተኛ የሆኑ መሰረታዊ ልዩነቶች ይታዩ ነበር። ይህም ልዩነት፣ ዛሬ የትጥቅ ትግል ይጀመር በሚሉና (በኋላ አለም አቀፍ ፌዴሬሽን የተባለው ድርጅት አቋም የሚያንጽባርቁ) በሌላ በኩል ደግሞ ለነቃ፣ ለተደራጀና ለህዝባዊ ጦር በሚሉ ይከፈላል። የልዩነቶቹ ዝርዝር “ ልዩነቶቻችን“ በሚል ርአስ በ1966 በብሮሹር መልክ ወጥቷል።
በ 1966፣ የየካቲት አብዮት ከፈነዳ በኋላ፣ በአኢተማና በአለም አቀፍ ፌዴሬሽን መሃከል የነበሩት ልዩነቶች በአገር ውስጥ በመኢሶንና በኢህአፓ የተንጸባረቁ ነበሩ።
በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር እስክ 1977 ዓ/ም ድረስ ዲሞክራሲ የሰፈነበት፣ ልዩ ልዩ ሃሳቦች የሚፋጩበት መድረክ በመሆን ቀጠለ። ነገር ግን፣ የማህበሩ አባላት የነበሩት ተማሪዎች፣ ትምህርታቸውን እየጨረሱ ወደ አገር እየገቡ በመምጣታቸው፣ ሌላው ደግሞ በየሃገሩ ሥራ እየያዘ በመሄዱ፣ በደርግ ዘመን ወደ ምዕራብ አውሮፓ የሚመጡት የተማሪዎች ቁጥር በጣም በመቀነሱ፣ በስደት የሚመጣው ሰው ቁጥር በመጨመሩና ችግሮቹ የተለያዩ በመሆናቸው፣ ማህበሩ እየተመናመነ መጣ።
በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር 25ኛውን የብር ኢዮቤሊዩ ጉባኤውን በስዊድን አገር ነሃሤ 1977 በስቶኮሆልም ከተማ አከበረ። ይህም የማህበሩ የመጨረሻ ጉባኤ ነበር።

ጥቅምት 1961 ዓ/ምTatek | ታጠቅ

ታህሳስ 1961 ዓ/ምTiglachin | ትግላችን

ሃምሌ 1961 ዓ/ምTatek | ታጠቅ

August/ነሃሴ 1961 አም (Eth)Tiglachin | ትግላችን

September/ታህሳስ 1962 አም (Eth)Tiglachin | ትግላችን

Octobre/ጥቅምት 1962Tatek | ታጠቅ


April-July/ሚያዝያ-ሃምሌ 1962 አምTiglachin | ትግላችን ቁ 3

December/ታህሳስ 1963 አምBrochure | ብሮሹር

December/ታህሳስ 1963 አምTatek | ታጠቅ

September/መስከረም 1964 አምTiglachin | ትግላችን ቁ 1

1963 አምTiglachin | ትግላችን ቁ 1

Nov/Dec ህዳር ትህሳስ 1965 አምTiglachin | ትግላችን ቁ 1

April/ሚያዝያ 1965 አምTatek | ታጠቅ

January/ጥር 1966 አምTiglachin | ትግላችን ቁ 1


January/ጥር 1966 አምTiglachin | ትግላችን ቁ 4

July/ ሓምሌ 1966 አምብሮሹር


October/ጥቅምት 1967 አምTiglachin | ትግላችን
