ስለ

እንኳን ወደ ነገደ ጎበዜ ቤተ መዝገብ  በደህና መጡ

ስለ

እንኳን ወደ ነገደ ጎቤዚ ማህደር ቦታ በደህና መጡ።

የመዝገብ ቤቶች አመጣጥ

በዚህ ድረ ገጽ ውስጥ ተሰባስበው የቀረቡት ጽሁፎች፣ በአብዝኛው ከነገደ የግል ማህደር የተገኙ ናቸው። ጽሁፎቹም አንዳንዶቹ በስሙ የተፈረሙ፣ አንዳንዶቹ በብእር ስም የወጡ ሌሎቹ ደግሞ ያልተፈረሙባቸው ይገኙበታል።

በጥንቃቄ የተመዘገበ ቅርስ።

የጽሁፎቹ አርእስትና ቀን ፣እንዲሁም ጽሁፉ የወጣበትን መጽሄት፣ ጋዜጣ፣ ድርጅት፣ ማህበር ወዘተርፈ፣ ዝርዝሩን መዝግቦ ስላስቀመጠው ፣ ጽሁፎቹን ማሰባሰብና ማቀናጀት ቀላል ነበር ማለት ይቻላል።

የቤተሰብ ግብር።

ድረገጹ የተዘጋጀው በቤተሰቡ ሲሆን የቀረበውም እንደ ግል ቤተ መዝገብ/ቤተ መጽሃፍት በዋናነት ለልጆቹና ለልጅ ልጆቹ፣ የአባታቸውን፣ የአያታቸውን ታሪክ እንዲያውቁት ለማስተላለፍ የታቀደ ነው።

ለተመራማሪዎች የሚሆን ምንጭ።

በተጨማሪ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪዎች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች ለሚያደርጉት ጥናት፣ምርምርም ሆነ ትንተና እንደ መረጃ/ ማገናዘቢያ (reference) በተወሰነ ደርጃ አስተዋጽኦ ያደርጋል በለን ተስፋ እናደርጋለን።

በትውልዶች መካከል የእውቀት ሽግግር

መረጃ ማሰባሰብና ተደራሽ ማድረግ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ እውቀትን ለማዳበር የረዳል የሚል ጽኑ እምነት አለን።

የአጠቃቀም እና የጥቅስ ውሎች።

በዚህ ድረ ገጽ ላይ የተሰበሰበውን ሰነድ ምንጩ እስከተጠቀሰ ድረስ ለትርፍ ላልሆነ ዓላማ መጠቀም ይቻላል። ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ "ከነገደ ጎበዜ የግል መዘገብ የተገኘ - www.negedegobezie.com" የሚለውን ሃረግ እንዲጨምሩ በትህትና እንጠይቃለን።

አመሰግናለሁ

ይህንን ድረ ገጽ ለማዘጋጀት፣ ሰነዶችን በማፈላለግ ለረዱን በዋሽንግተን ዲሲ፣ በስዊድን፣ በጀርመን፣ በቤልጅየም፣በኢትዮጵያ ለሚገኙት ወዳጆቻችንን የልብ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።

Negede Gobezie

Privacy Preference Center